OpenStreetMap

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው

OpenStreetMap ምንድን ነው?

Open Street Map (ነፃ ፈጣን የዓለም ካርታ) ማለት ነፃ እና ፈጣን የሆነ የዓለም ካርታን ለማዘጋጀት አላማው አድርጎ የተነሳ ፕሮጀክት ነው፡፡ የሚሰበሰቡት አለም አቀፍ መረጃዎች የሚያተኩሩትም በመንገዶች በባቡር መስመሮች ፣ በወንዞች ፣ በደኖች ፣ በመኖሪያ ስፍራዎች እና ሌሎች በካርታ ላይ የምናያቸው ሲሆን ምክንያቱም መርጃዎቹም አሁን ካሉት ካርታዎች ላይ ሳይሆን በቀጥታ የሚሰበሰቡ ናቸው ለእነዚህም መረጃዎች ባለመብቶች ነን። የነፃ ፈጣን የአለም ካርታ መረጃዎቹ ሙሉ በሙሉ የመጠቀም ፈቃድ የማያስከፍሉ ናቸው።

ለምን አንተ/አንቺ?

በአሁኑ ወቅት ነፃ እና ፈጣን እንዲሁም አለም አቀፍ የሆነ የጂኦግራፊካዊ መረጃ ማግኘት በጣም ከባድ ነው፡፡ ምንአልባት የሀገር ውስጥ ካርታ በድረ-ገፅ ወይም በህትመት ይዘት በአብዛኛው በግዢ (አንዳንዴም በውድ ዋጋ) ለባለቤትነት ፍቃድ ማስረጃ ያስከፍላል። ይህ በተመሳሳይ መልኩ ለምርምርና ለማስተማር ክፍያ ይጠየቅበታል። ነፃ ፈጣን የአለም ካርታ የሚሸጡ መረጃዎች ላይ ያለውን ጥገኝነት በማስቀረት ሙሉ የፈጠራ እንቅስቃሴዎችን እንዲሁም በአባላቱ በመተባበር ነፃ መረጃዎችን በማጠናቀር ለአለም ህዝብ ያቀርባሉ።

አንድ ተጉአዥ ቡድን ካርታዎችን (ኤሌክትሮኒክስ ወይም የታተመ) ለጉዞ ለመጠቀም ቢፈልግ ወይም ከፍተኛ ገንዘብ ቢከፈልም ከገዛው በሁዋላ በካርታው ላይ የተካተተው መረጃ ያልተማላ ወይም ጊዜው ያለፈበት ሊሆን ይችላል።

ነፃ ፈጣን የዓለም ካርታ ከሶስተኛ ወገን በተገኙ መረጃዎች መተማመን ብዙ ጉዳቶች ያሉት መሆኑን ስለተገነዘበ ሙሉ ብሙሉ ትኩረቱን በአዳዲስ ፈጠራዎች ላይ አዙሮዋል። ምንም እንኩዋን የአባላቶቹ ትብብር ነፃ የሆነ የመረጃ ጥርቅም ቢሆንም የሁሉም አለማትን ስብስቦች ለመጠቀም ይሞክራል።

የጎግል ካርታ ነፃ አይደለም እንዴ?

የጎግል ካርታዎች (የሌሎች አገልግሎት ሰጪዎችን ጨምሮ) ነፃ ሲሆኑ ነፃ ያልሆኑ ናቸው፡፡ ጎግል በካርታዎቹ አጠቃቀም ላይ ያለውን ቅድመ ሁኔታዎች አሁንም መጠቀሙን እንደቀጠለ ነው፡፡ በመረጃ መረብ (Internet) ላይ የሚገኙት የመረጃ መረብን ወይም የአገልግሎት ሰጪዎችን (API) የሚጠቀሙ ናቸው፡፡ እንዲያውም አንዳንዴ ይህን ካርታ አባዝቶ ማስተም እና ማሰራጨት ክልክል ነው፡፡

በተጨማሪም የጎግል ካርታ ለሁሉም ክፍት ቢሆንም ካርታው የተጠናቀረበት መረጃን ማግኘት የማይታሰብ ነው፡፡ ካርታዎቹን መጠቀም የሚቻለው ባሉበት እና ለተጠቃሚ ክፍት እንዲሆኑ በተደረጉበት ሁኔታ ብቻ ነው፡፡ ካርታዎቹን በሌላ መልኩ ወይም የራስ የሆኑ የጉዞ መረጃዎች ቢኖሩም ከዛ ያለፈ ነገር ማደረግ አይቻልም ነገር ግን የነፃ ፈጣን የአለም ካርታ ፕሮጀክት ጥሬውን እና ካርታው የተጠናቀረበት ማረጃ ማንኛውንም ሰው በሚፈልገው መልኩ መጠቀም እንዲችል ክፍት አድርጎታል፡፡

እንዴት አባል መሆን ይቻላል?

አብዛኛዎቹ የፐሮጀክቱ አባላት በጂ.ፒ.ኤስ (GPS) በመታገዝ የካርታ መረጃን ይሰበስባሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ የፀደቁ የአየር ፎቶግራፎችን እና የተሟሉ መረጃዎችን በቦታው ላይ በመሳል ያግዛሉ፡፡ አነስተኛው ድጋፍም ቢሆን ለፕሮጀክቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ያለህበት/ያለሽበት (የምታውቀው/የምታውቂው) ቦታ ሙሉ በሙሉ ተሰርቷል? ወይስ ልታሻሽለው/ሽይው የሚገባ ስህተት አለ? ለፖስታ አገልግሎት ድርጅት ቅርበት አለህ/ሽ እንዲሁም የቤት ቁጥሮችን በቃል ታውቃለህ/ታውቂያለሽ?

በፕሮጀክቱ ላይ የሚሳተፉ የኮምፒውተር ፕሮግራመርስ ለማዕከላዊው የመረጃ ማጠናቀሪያ ክፍሎች፣ ለአራሚዎች፣ ለካርታ ሰዓሊዎች፣ ለሶፍትዌር ባለሙያዎች እንዲሁም ለተባባሪ ኮምፒውተር ፕሮግራመርስ እገዛ ስለሚያደርጉ በየጊዜው ይበረታታሉ፡፡

የፕሮጀክቱን መረጃዎች ለመጠቀም ሞክረህ/ሽ ታውቃለህ (ታውቂያሽ) ወይስ የአየር ፎቶግራፎቹን፣ ከተሰሩ ረጅም ጊዜ ያስቆጠሩ ካርታዎችን (ምናልባትም የመጠቀሚያ ጊዜ ፈቃድ ያለፈባቸው) ወይም የጂ.ፒ.ኤስ (G.P.S) የአገልግሎ ሰጪዎችን የጉዞ ጠቋሚ መረጃዎችንስ ለማየት ሞክረሃል/ሻል ይህ ከሆነ መረጃዎቹን አንድ ቦታ ላይ ልንጠቀምበት እንችላለን።

በፕሮጀክቱ እንዴት መሳተፍ እንደሚቻል ጠለቅ ብለው ይመልከቱ

How to help in the Wiki

እንዴት አባል መሆን ይቻላል?

በጂ.ፒ.ኤስ. የሚሰበሰቡት መረጃዎች አንደኛው የፕሮጀክቱ መረጃ ክምችት የሚማላበት መንገድ ቢሆንም ብቸኛው ግን አይደለም። ጂ.ፒ.ኤስ ባይኖርህም/ሽም በሌሎች የመረጃ አጠነቃቀር ስራዎች ወይም ተሰርተው ባለቁት ቦታዎች ላይ ባለሽ/ህ የግል እውቀት በመመርኮዝ ድጋፍ ማድረግ ትችላለህ/ትችያሽ

መረጃዎቹን እንዴት መጠቀም እችላለሁ?

ያሉትን መረጃዎች ለማየትም ሆነ በፍጥነት ለመዳሰስ እንዲሁም በፕሮጀክቱ ላይ ያሉትን ቅድመ-ቀመር የተሰራባቸውን ምስሎች (በopenstreetmap.org.et ላይ የተካተተውን ጨምሮ) ካርታዎቹ ለአጠቃቀም ቀላል ሆነው የተዘጋጁ ናቸው፡፡

በመርጃ ካርታዎቹ ላይ የተሰሩ የራሳቸው የሆነ ቀመር ወይም የግላቸው አሰራር ለማንፀባረቅ የፈለጉ የሚያመርቱት ከጥሬ መረጃው ይልቅ ምስሎቹን በመጠቀም ነው፡፡ ጥሬ መረጃውን ‹‹Planet file›› የተሰኘውን የአለም መረጃን ጨምሮ ወይም ከዛ ላይ የተውጣጡትን ነጠላ የሆኑ የተለያዩ የአውሮፓ አገራትን መረጃዎች ጨምሮ) ወቅታዊ በሆነ መልኩ ማግኘት እንዲቻል ሆኖ የተዘጋጀ ነው፡፡ አነስተኛ ለሆኑት (እስከ 100 ኪ.ሜ ስኬዌር ወይም በመረጃ ስብሰባ አነስተኛ ለሆኑ አከባቢዎች) ጥሬ መረጃዎችን በቀጥታ www.openstreetmap.org ወደተሰኘው የኢንተርኔት ድር ገጽ በመሄድ ማግኘት ይችላል፡፡

የመስሪያ ፈቃዱ ምን አይነት ነው?

ሁሉምመረጃ ‹‹Creative Commons Attribution-Share Alike 2.0›› የስራ ፈቃድ ስር ነው፡፡ ፈቃዱ ሁሉም አይነት የመረጃ አጠቃቀምን የሚፈቅድ ሲሆን ከዛ ባሻገር ግን ምንጩን መጥቀስ እና የተደረገውን የመረጃ ለውጥ በዚሁ ፈቃድ ስር በማድረግ መጠቀምን ይጠይቃል፡፡

Legal FAQ.

መርጃዎቹ ምን ያህል የተሟሉ (ሙሉ) ናቸው?

በመጀመሪያ የተሟሉ (ሙሉ) የሚለውን ቃል ፍቺ እንሰጠው፡፡ ሙሉ (የተሟላ) ማለት ምን ማለት ነው? ወይስ ሁሉንም ዋና እና በመንግስት የታወቁ መንገዶችን የያዘ ማለት ነው? ወይስ ሁሉንም የብስክሌት (የሳይክል) ወይም የቤት ለቤት የፖስታ አድራሻቸውን የያዘ? ካለሆነስ ሁንም የቤት ቁጥር እና የመናፈሻ ወንበሮችን ያካተተ ማለት ይሆን? የፕሮጀክቱ አከባያዊ (ክልላዊ) መረጃ ዝርዝሩ በጣም የተለያዩ ነው፡፡

ማንኛውንም ሰው የኛን መረጃ ባለበት ሁኔታ ከተጠቀሙበት ወይም ለታቀደለት አለማ እንደምስል ካገለገለው ‹‹በበቂ ሁኔታ የተሟላ ሙሉ›› ነው ለማለት ያስችላል፡፡ ካልሆነም ደግሞ ከአንድ ወር በሁዋላ በድጋሚ ይሞክሩ።

በፕሮጀክቱ ውስጥ ምን ያህል ሰዎች ይሳተፋሉ?

በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ በአለም ላይ (ከሚያዚያ 2008 ጀምሮ) ወደ 70,000 ሰዎች የፕሮጀክቱ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ባለፈው ወር 10 ገደማ ያሉት ብቻ ናቸው በንቃት እየተሳተፉ ያሉት፡፡ በአሁኑ ወቅትም የተሳታፊዎቹ ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው።

wiki ገፅ ላይ ያለውን ስታትስቲካዊ መረጃ ይመልከቱ፡፡

የገቢ ምንጩ ከየት ነው?

ሁሉም የፕሮጀከቱ ስራዎች የሚካሄዱት የማግኘት አለማ በሌለባቸው የበጎ ፈቃደኛ ሰራተኞች ነው፡፡ ቁልፉ የሆኑ አገልግሎተች እንዲሁም የመረጃ ክምችቱ የሚካሄደበት ዋናው የኮምፒውተር መሣሪያ (ሰርቨር) የሚንቀሳቀሰው በግማሽ ስፖንሰር ተደርጎ በግማሽ ደግሞ ፍላጎቱ ያላቸው የፕሮጀክቱ አባላት ከኪሳቸው በሚያወጡት ገንዘብ ነው፡፡ በብሪታንያ ደግሞ የነፃ ፈጣን የአለም ካርታ ማህበር (OpenStreetMap Association) እንዲሁም የነፃ ፈጣን የአለም ካርታ ተቋም (OpenStreetMap Foundation) የሚባሉ ሁለት ድርጅቶች አሉ፡፡ ይህም የድጋፍን አነስተኛ መጠን የሚሸፈን ነው፡፡ ነጠላ የሆኑ ዝግጅቶች የሚካሄዱት አልፎ አልፎ ፍላጎት ባላቸው መሰሪያ ቤቶች ድጋፍ ነው፡፡